በቅርቡ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አለመረጋጋት ሚልዮኖችን ወደ ረሃብ አጋልጧል። የተለያዪ የእርዳታ ድርጅቶችህ እንደ ዱቄት፣ዘይት፣እና ሱኳር ያሉ የጊዝያዊ ምግብ አቅርቦት ላይ እየሰሩ ይገኛሉ። የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለመከላከል ወሳኝ የሆኑት አትክልቶች ግን በአሁኑ ሰአት ቀልብ አላገኙም። በገበረዎች መጪ፣ የኢኮኖሚ ማቋቋም እና መረጋጋት ላይ ኢንቨስት እንድታደርጉ ጥርያችንን እናቀርባለን።
1000 ካሬ ሜትር መሬት 40-50 ኩንታል ምግብ በአንድ የምርት ወቅት ማፍራት ይችላል። 1000 ካሬ ሜትር መሬት ለማልማት ደግሞ 100 ዶላር ያስፈልጋል። ይህ ማለትም በ100 ዶላር፤ 25 ሰዎችን አመቱን ሙሉ ሊመግብ የሚችል በቂ ምግብ ማፍራት እንችላለን። የምትችሉትን ያህል እንድታበረክቱ ጥርያችህንን እናቀርባለን።
ይህ መርሃ ግብር ቀጣይነት ወዳለው የገንዘብ ማሰባሰብ፣ ለገበሬዎች የፋይናንስ ድጋፍ ወደ ማቅረብ፣ የግል ዘርፍ እድገት እና የእርሻ ዘርፉ መልሶ የማቋቋም ስራዎች እንደሚስፋፋ ተስፋ እናደርጋለን። ይህ መርሃ ግብር ዝርያ እና ሌሎች የእርሻ ግባቶች፣ የመስኖ ልማት መሳርያዎች እና ማሽነሪዎች ለማቅረብ ያለመ ነው። የረዥም ግዜ እቅዱ ትግራይ ውስጥ የእርሻ ልማት እርዳታ ማቋቋም እና የኢንቨስትመንት ዘርፉ ማገዝ ነው።